በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ነጥብ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ሃዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የምስራች ፈለቀ በ57ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረችው ጎል ሃዋሳ ከተማን መሪ አድርጓል።
ምህረት አለሙ በ67ኛው ደቂቃ ላይ ያሳረፈችው ግብ አርባምንጭ ከተማ አቻ ሆኗል።
ውጤቱን ተከትሎ ሃዋሳ ከተማ በ22 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዛሬ በተደረጉ በሌሎች ጨዋታዎች የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይርጋጨፌ ቡና 4 ለ 0 ሲያሸንፍ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ረቷል።