በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪነቱን ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ይርጋጨፌ ቡናን 4 ለ 0 ረቷል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ትዕግስት ያደታ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እየሩሳሌም ወንድሙ እና ማህሌት ምትኩ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ30 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በ10 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።