በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሸገር ከተማ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰርካለም ባሳ በ79ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።
በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ18 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በዘጠኝ ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።