የሊጉ መሪ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 24/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል።
አርሰናል በ30 ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል። ብሬንትፎርድ በ19 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
መድፈኞቹ ካሸነፉ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ያላቸውን የንጥብ ልዩነት በድጋሚ ወደ አምስት ከፍ ያደርጋሉ።
በሌሎች መርሃ ግብሮች ሊድስ ዩናይትድ ከቼልሲ እና ሊቨርፑል ከሰንደርላንድ በተመሳሳይ ከምሽቱ 11 ሰዓት ከ15 ላይ ይጫወታሉ።
ብራይተን ከአስቶንቪላ፣ በርንሌይ ከክሪስታል ፓላስ እና ዎልቨርሃምፕተን ዎንድረርስ ከኖቲንግሃም ፎረስት በተመሳሳይ ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።