በተጠባቂው ጨዋታ ባርሴሎና አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ባርሴሎና አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ ሳምንት የ15ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባርሴሎና አትሌቲኮ ማድሪድን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በካምፕ ኑ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ራፊኒያ፣ ዳኒ ኦልሞ እና ፌራን ቶሬስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
አሌክስ ባኤና ለአትሌቲኮ ማድሪድ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው ላይ ባርሴሎና ያገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ሮበርት ሌዋንዶስኪ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በሊጉ 12ኛ ድሉን ያስመዘገበው ባርሴሎና በ37 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። ከተከታዩ ሪያል ማድሪድ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አትሌቲኮ ማድሪድ በ31 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
በ33 ነጥብ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ ነገ ከሜዳው ውጪ ከአትሌቲኮ ቢልባኦ ጋር ያደርጋል።