ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኑ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበረከተ - ኢዜአ አማርኛ
ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድኑ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተበረከተ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ):- የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለአፍሪካ ዋንጫ ላለፈው ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የ10 ሚሊዮን ብር የገንዝብ ሽልማት አበርክቷል።
ሚኒስቴሩ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድኑ ማምሻውን የእራት ግብዣ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ በመርሐ ግብሩ ላይ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ለብሄራዊ ቡድኑ ያበረከተ ሲሆን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የገንዘብ ሽልማቱን አስረክበዋል።
ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በወቅቱ የተገኘው ስኬት የመንግስትና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጋራ ስራ ውጤት እንደሆነ ተናግረዋል።
ብሄራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫው ተሳትፎው ውጤታማ ጊዜ እንዲያሳልፍ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ እና ሌሎች የፌዴሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ ዛሬ ከኬንያ አቻው ጋር ባደረገው የደረጃ ጨዋታ 3 ለ 0 በማሸነፍ ለአህጉራዊው መድረክ ማለፉን አረጋግጧል።
ብሄራዊ ቡድኑ ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ይመለሳል።
ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ውድድር ላይ ስትሳተፍ የሞሮኮው ለአራተኛ ጊዜ ነው።