ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ነጌሌ አርሲ እና ሸገር ከተማ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሐግብር  ነጌሌ አርሲ እና ሸገር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። 

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ጀቤሳ ሚኤሳ በ55ኛው እና በ70ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች ሸገር ከተማ መሪ ሆኖ ነበር። 

ይሁንና ከቤ ብዙነህ በ75ኛው እና ሮሆቦት ሰላሎ በ93ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፏቸው ጎሎች ነጌሌ አርሲን አቻ አድርገዋል። 

ውጤቱን ተከትሎ ነጌሌ አርሲ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ሸገር ከተማ በዘጠኝ ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።

ጨዋታውን ተከትሎ የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።  

የዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም