ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያካሄደውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።
በጨረታ ሂደቱ 17 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን በዚህም የምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ በአማካኝ 154 ነጥብ 3993 ብር ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
ቀጣዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።