ቀጥታ፡

በከተሞች መሰረተ ልማትን በማሟላት ለነዋሪዎች ምቹ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል - ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ

ከሚሴ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፡-በሀገሪቱ ከተሞች መሰረተ ልማትን  በማሟላት ለነዋሪዎች እና ለኢንቨስትመንት  ምቹ የማድረጉ ተግባር  ተጠናክሮ  የሚቀጥል  መሆኑን  የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር  ጫልቱ ሳኒ ገለጹ። 

ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች  የፌዴራል  ከፍተኛ አመራሮች በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከሚሴና ጨፋ ሮቢት ከተሞች የልማት ሥራ እንቅስቃሴዎችን ዛሬ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።


 

በጉብኝቱ ወቅት ሚኒሰትሯ እንዳመለከቱት፤ በከተሞች የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረት ልማት ግንባታዎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። 

በሀገሪቱ ከተሞች መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ለነዋሪዎች እና ለኢንቨስትመንት  ምቹ የማድረጉ ተግባር  ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተጀመሩ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውንና ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ምክረ ሀሳብ  አቅርበዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው ፣ በዞኑ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በዞኑ ከተሞችም መሰረተ ልማትን በማሟላት ለነዋሪዎች፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

በጉብኝቱም የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል። 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም