ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፀጋ ከድር በ43ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ15 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 3ኛ ከፍ  አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ በውድድር ዓመቱ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።


 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሃ ግብር መቻል እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

አብዱልከሪም ወርቁ ለመቻል፣ መሐመድኑር ናስር ለድሬዳዋ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በጨዋታው ኢሞሮ ማናፍ ከመቻል እና አቡበከር ሻሚል ከድሬዳዋ ከተማ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ13 ነጥብ 5ኛ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ በ11 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ምሽት 12 ሰዓት አዲስ አዳጊዎቹ ነጌሌ አርሲ እና ሸገር ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም