ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በማለፏ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ በማለፏ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በመልዕክታቸው ይህ እግር ኳስ ወዳድ ለሆነው ህዝባችን ትልቅ የድል ብስራት ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን (ቀይ ቀበሮዎቹ) ኬንያን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከ22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፋቸው እንኳን ደስ አለን ሲሉም ገልጸዋል።
በስፖርቱ ዘርፍ ታዳጊዎች ላይ በርትተን ከሰራን እግር ኳሳችን በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ መድረኮች ከፍ የሚልበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ይህ ስኬት አመላካች ነው መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዛሬው ውጤት እንዲገኝ የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።