በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ ከፉልሃም ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ ከፉልሃም ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።
በዛሬው ዕለትም ሶስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ማንችስተር ሲቲ ወደ ክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም በማምራት ከፉልሃም ጋር ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
ሰማያዊዎቹ በ25 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። ፉልሃም በ17 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ማንችስተር ሲቲ ካሸነፈ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ ሁለት ዝቅ ያደርጋል።
በሌሎች መርሃ ግብሮች ቦርንማውዝ ከኤቨርተን ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ30፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ይጫወታሉ።
የሊጉ የ15ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሕዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።