ቀጥታ፡

የ2018 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 22/2018(ኢዜአ)፦የ2018 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ከዛሬ ህዳር 22/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ጣቢያዎች በመካሄድ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል። 

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ መጀመሩን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን፤ ምዝገባው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

ለሐጅ ጉዞ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ቀነ ገደብ መመዝገብ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም