ምድረገነት ሽሬ በሊጉ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ምድረገነት ሽሬ በሊጉ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ምድረገነት ሽሬ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ማሙሽ በ34ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ምድረገነት ሽሬ በ12 ነጥብ ከ10ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ከፍ ብሏል።
በአንጻሩ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ13 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።