በተጠባቂው ጨዋታ ቼልሲ እና የሊጉ መሪ አርሰናል አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ቼልሲ እና የሊጉ መሪ አርሰናል አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታ ቼልሲ እና አርሰናል አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ትሬቮህ ቻሎባህ በ48ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ቼልሲ መሪ ሆኗል።
ሚኬል ሜሪኖ በ59ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል አርሰናል አቻ መሆን ችሏል።
በጨዋታው ላይ የቼልሲው የአማካይ ተጫዋች ሞሰስ ካይሴዶ በ38ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል። ይህም በቡድኑ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ አሳድሯል።
አርሰናል በጨዋታው ላይ ያገኘውን የቁጥር ብልጫ በሚገባ መጠቀም አልቻለም።
ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ24 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 30 ከፍ አድርጓል።
ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ዝቅ ብሏል።
ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል ዌስትሃም ዩናይትድን 2 ለ 0፣ ማንችስተር ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
ብራይተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲረታ አስቶንቪላ ዎልቭስን 1 ለ 0 አሸንፏል።