ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ጨዋታው ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሄዷል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ15 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው አዳማ ከተማ በበኩሉ በ13 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን በመሳይ አገኘሁ የፍጹም ቅጣት ምት 1 ለ 0 አሸንፏል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቀሌ 70 እንደርታን 1 ለ 0 በመርታት በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል። ጌትነት ተስፋዬ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።

በጨዋታው ዳዊት ገብሩ በሁለት ቢጫ ካርድ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በሌላኛው መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ዳግም አወቀ ለፋሲል ከነማ ፣ መሳይ ሰለሞን ለወላይታ ድቻ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የፋሲል ከነማው ቃልኪዳን ዘላለም በ23ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም