ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል። በክፍል ሁለት ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል… - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል። በክፍል ሁለት ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል…
የሀገራዊ ብልጽግና አእማዶች የተባሉት ኢኮኖሚ (ከሁሉም ለሁሉም በሁሉም)፣ ፖለቲካ (አካታችና አሳታፊ) እና ማኅበራዊ (ትውልዳዊ ልማት) ናቸው።
በችግር ትብታብ ታስረን እንዳንቀር ተስፈንጥረን ወደምንፈልገው ነገር እንድንደርስ በአንዳንድ ጉዳይ ላይ መደመራዊ ዝላይ አስፈላጊ ነው።
መደመራዊ የዝላይ መንገድ ዋና ዋና ዓላማዎች ከቀዳሚው ጋር ያለ ልዩነትን በፍጥነት ማጥበብ እና እመርታዊ እድገት ማምጣት ናቸው።
የትውልድ ግንባታ ስትራቴጂዎች የሚባሉት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ ዲጂታል ዓርበኝነት፣ የትምህርት ተሃድሶ እና የባህል ኢንዱስትሪ ናቸው።
ማስተካከል፣ ማስፋፋት እና ማበርከት የመደመር ትውልድ መርሆዎች ናቸው።
የመደመር መንግሥት እንቅፋት - ሐሳብ አልቦነት ነው። ሐሳብ አልቦነት ማለትም በሕዝበኝነት መታወር እና መስከር፤ በነባር ባህል መታጠርና መታሰር ፤ በጊዜያዊ ችግር መሸበርና መሰበር ማለት ነው።
የሐሳብ ሉዓላዊነት- የመደመር አሸናፊነት ነው።በዚህም መሠረት አመክኗዊ ውይይትና ሙግት፣ ሚዛናዊ ትብብርና ፉክክር፣ ሐሳብን በወረቀት - ሥራን በመሬት መሆን አለበት።
ፍሪሊዮን - የመደመር ቀመር ነው። ይህ ማለትም መስጠትና አገልግሎት፣ ሰውን ማትረፍና ማብቃት፣ ወደ ሰላምና ብልጽግና፣ ስለ ሀገርና ትውልድ እንዲሁም ሐሳብና ሰው በተቋም ማለት ነው።