የኢዜአ ጋዜጠኛ ጌትነት ሸንቁጤ በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማትን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢዜአ ጋዜጠኛ ጌትነት ሸንቁጤ በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ የሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ጋዜጠኛ ጌትነት ሸንቁጤ በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የ2025 የሚዲያ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።
ሽልማቱን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እጅ ተረክቧል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የ2025 የሚዲያ ሽልማት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ነው።
የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመድረኩም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኛ ጌትነት ሽንቁጤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የ2025 የሚዲያ ሽልማት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ አሸናፊ በመሆን ሽልማቱን ተቀብሏል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ የተለያዩ ሰፋፊ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል።