ማንችስተር ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
አዲስ አበባ፤ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፡-በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 በማሸነፍ ደረጃውን ያሻሻለበትን ውጤት አስመዝግቧል።
በክሪስታል ፓላስ ሜዳ ሴልኸርስት ፓርክ በተደረገው ጨዋታ ለዩናይትድ ዚርኪዜ እና ማውንት ከእረፍት መልስ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ድል ማድረግ ችሏል።
የፓላስን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ማቴታ በ36ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በ21 ነጥብ 6ኛ እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ በ20 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
የዕለቱ መርሐ-ግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ፤ ዌስትሃም ከሊቨርፑል፣ አስቶንቪላ ከዎልቭስ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከብራይተን በተመሳሳይ 11 ሠዓት ከ5 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቸልሲን ከአርሰናል ያገናኘው የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ ይደረጋል።