የመደመር መንግሥት በአራት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያጠነጥናል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የመደመር መንግሥት በአራት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያጠነጥናል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፡- የመደመር መንግሥት መፍጠር፣ መፍጠን፣ ማብዛት እና ማጥራት በሚሉ መሠረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚያጠነጥን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።
“በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሰጥተዋል።
በዚሁ ወቅትም፤ የመደመር መንግሥት ሲባል አራት መሠረታዊ ጉዳዮች ማለትም መፍጠር፣ መፍጠን፣ ማብዛት እና ማጥራት የሚሉትን ነጥቦች እንደሚይዝ አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ብዙ ያልፈጠረ ጥራትን ማረጋገጥ እንደማይችል አስረድተዋል።
ጥራት ያላቸው ጉዳዮች የሚወጡት ከብዙ ፈጠራ ውስጥ መሆኑንም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ብዙ ለመፍጠር ፍጥነት እንደሚያስፈልግም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስረዱት።
ያልፈጠነ ሰው ባለው ጊዜ በርከት ያሉ ጉዳዮች መፍጠር እንደማይችልም አመላክተዋል።
ብዙ ስንፈጥር ብዙ ስንሮጥ ከእነዚያ መካከል ጥቂቶቹ ረዘም ላለ ጊዜ ለመጓዝ ጥራትን ከዚያ ውስጥ መዝዞ ለማውጣት ያግዛል ማለት ነው ሲሉም አብራርተዋል።
ብዙ በመፍጠር ብሎም ብዙ ለመፍጠር በመፍጠን ነው ጥራትን የምናረጋግጠው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በስልጠናው ወቅት።
በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት የሚያጠነጥነው በእነዚህ እሳቤዎች ዙሪያ መሆኑንም ነው በአጽንኦት ያስገነዘቡት።