ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ዳግም አወቀ በ43ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ፋሲል ከነማን መሪ አድርጓል።

መሳይ ሰለሞን በ51ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፋት ግብ ወላይታ ድቻ አቻ ሆኗል።


 

የፋሲል ከነማው ቃልኪዳን ዘላለም በ23ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ በ16 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የሊጉን መሪነት ከሲዳማ ቡና የመረከብ እድሉን አልተጠቀመበትም።

ወላይታ ድቻ በስድስት ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም