ቀጥታ፡

ታንዛንያ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ታንዛንያ ኬንያን 3 ለ 1 አሸንፋለች። 

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ንሂንጎ ሉዜሌንጋ፣ ሉክማን ምባላሳሉ እና ሶአን ሻባኒ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አርምስትሮንግ ኦሞንዲ ለኬንያ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ታንዛንያ ውጤቱን ተከትሎ ወደ ፍጻሜ አልፋለች።

በተጨማሪም እ.አ.አ በ2026 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞንን ወክላ ያለፈች የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች።

ተሸናፊዋ ኬንያ ሶስተኛ ደረጃን ለማግኘት ትጫወታለች።

በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር አዘጋጇ ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ኢትዮጵያ ካሸነፈች ለአፍሪካ ዋንጫ ታልፋለች።

በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም