ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል አዳማ ከተማን አሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል አዳማ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። 

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተካሄደው ጨዋታ ቤተልሄም መንታሎ፣ ትዕግስት ወርቁ እና ጽዮን ፈየራ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

መቻል በ17 ነጥብ አራተኛ ድሉን በማስመዝገብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በሰባት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

አዳማ ከተማ በ10 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በሌላኛው መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በረድኤት አስረሳኸኝ ግቦች ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት በ19 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በአራት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም