ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ አራተኛ ድሉን አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ይርጋጨፌ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፊርማዬ ከበደ እና ሰርክአዲስ ጉታ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዘሪቱ ብርሃኑ ለይርጋጨፌ ቡና ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከተማ በ12 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 7ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ይርጋጨፌ ቡና በ10 ነጥብ ከነበረበት ሰባተኛ ደረጃ ወደ ስምንተኛ ዝቅ ብሏል።

ዛሬ በተደረገ የዘጠነኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም