የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስታንዳርድ ባንክ ተወካይ ጽህፈት ቤትን የሥራ ፈቃድ አደሰ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስታንዳርድ ባንክ ተወካይ ጽህፈት ቤትን የሥራ ፈቃድ አደሰ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተሻሻለው የባንክ ሥራ አዋጅ መሠረት በአዲስ አበባ ለሚገኘው የስታንዳርድ ባንክ ተወካይ ጽህፈት ቤት አዲስ የሥራ ፈቃድ በይፋ ሰጥቷል።
በአዲሱ አዋጅ መሠረት የውጭ ባንኮች ተጠሪነት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሆኗል።
በዚሁ መሠረት ከአሁን በኋላ የውጭ ባንኮች ተወካይ ጽህፈት ቤቶችን ፈቃድ የሚያድሰው እና አሠራራቸውንም በበላይነት የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንኩ ይሆናል።
ይህ ተግባር እና ኃላፈነት ቀደም ሲል ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተሰጠ እንደነበር ይታወቃል።
ከአሁን በኋላ የሚመጡ አዲስ ማመልከቻዎችን መርምሮ ፈቃድ መስጠትም በአዲሱ አዋጅ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊነት መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።
የተወካይ ጽህፈት ቤቶች ሚና የገበያ ጥናት ማካሄድ፣ ማስተዋወቅ እና ትስስር መፍጠር ብቻ በመሆኑ፤ የባንክ አገልግሎት የመስጠት ስልጣን የሌላቸው መሆኑም ተመላክቷል።