በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 19/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የዘጠነኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቅድስት ቴቃ፣ ታሪኳ ጴጥሮስ፣ የምስራች ላቀው እና መሰሉ አበራ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ቢታኒያ አሰረፍ ለሲዳማ ቡና ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ21 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በዘጠኝ ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከይርጋጨፌ ቡና በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ይጫወታሉ።