ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2028 የሚካሄደውን 96ኛውን የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመረጠች

አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2028 የሚካሄደውን 96ኛውን የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እንድታዘጋጅ በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች።


 

ኢትዮጵያ ጠቅላላ ጉባኤውን እንድታዘጋጅ በሙሉ ድምጽ የተመረጠችው በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ ሲካሄድ በቆየው 93ኛ የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።


 

ከሦስት ወር በፊት እ.ኤ.አ 2025 በነሐሴ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ በተካሄደው 26ኛው የኢንተርፖል አፍሪካ ሪጅናል ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን 27ኛውን የኢንተርፖል አፍሪካ ሪጅናል ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ መመረጧ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም