ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቀሌ 70 እንደርታ ሀዲያ ሆሳዕና ከአርባምንጭ ከተማ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ተካሄደዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ  መቀሌ 70 እንደርታ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ኪቲካ ጅማ እና ሱሌይማን ሀሚድ ለመቀሌ 70 እንደርታ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አዲስ ግደይ እና ኤፍሬም ሌጋሞ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎሎቹን ከመረብ ላይ ያሳረፉ ተጫዋቾች ናቸው።


 

መቀሌ 70 እንደርታ በሶስት ነጥብ 19ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ10 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው  ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ከአርባምንጭ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

እዮብ አለማየሁ ለሀዲያ ሆሳዕና እና ታምራት እያሱ ለአርባምንጭ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሀድያ ሆሳዕና በሰባት ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።


 

አርባምንጭ ከተማ በአራት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ በውድድር ዓመቱ አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም።

ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የሊጉ ጨዋታ ምድረገነት ሽሬ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።

የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሕዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም