ቀጥታ፡

 ህብረ ብሄራዊ አንድነትን  ለመገንባት የሕዝቦችን የእርስ በእርስ ትስስር ማጠናከር ላይ ትኩረት ተደርጓል 

ሚዛን ፤ ሕዳር 18/2018(ኢዜአ)፦ ብዝሀነትን ለማጎልበትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን  ለመገንባት የሕዝቦች የእርስ በእርስ ትስስር ማጠናከር ላይ ትኩረት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት አስታወቀ።

"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ 20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በክልል ደረጃ ሚዛን አማን ከተማ በፓናል ውይይት ተከብሯል።


 

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ጌታቸው ኬኒ እንዳሉት፤ በሕዝቦች መካከል መቀራረብን ለማጠናከር የቀኑ መከበር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው።

ብዝሀነትን ለማጎልበትና ህብረ ብሄራዊነት ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ለማጽናት የህዝቦችን የእርስ በእርስ ትስስር ማጠናከር  ላይ ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል።


 

ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችንን በአግባቡ መጠቀምና ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ድሎችን  በጋራ በመከወን እንደሃገር የተያዘውን የብልጽግና ጉዞ ማሳካት ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ብሔረሰቦች ባህል፣ ቋንቋና ወግ እንዲለማ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በበኩላቸው፤ አንድነት ኃይል መሆኑን ተገንዘብን በኅብረት መቻልን በተለያዩ ፕሮጀክቶች እያሳየን ነው፣ ወደ ፊትም እንቀጥላለን ብለዋል።


 

በዞኑ የሕዝቦች የእርስ በእርስ ትስስር በአብሮነትና መቻቻል እሴት ላይ ተመሥርቶ በሁሉም የልማት ዘርፎች በአንድነት በመቆም ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ከበዓሉ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ጉጣ ብዙአየሁ፤ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዘቦች  ቀን መከበር የተለያዩ ባህሎችን ወደ አደባባይ በማውጣት የኢትዮጵያን ቱባ ባህል ለዓለም እንዲታይ አስችሏል ብለዋል፡፡


 

 ወይዘሮ ደብሪቱ ኃይሉ በበኩላቸው፤ የጋራ እሴቶቻችንን በማጎልበት አብሮነታችንን እናጠናክራለን ብለዋል ።


 

ልዩነቶችን ውበት በማድረግና መቀራረብን በማጠናከር አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ እናተኩራለን ሲሉም አክለዋል ።

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ቀን ፍትኃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ነው ያሉት ደግሞ ከጋምቤላ ክልል በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊ አቶ  ጆንማያንግ ኩን ናቸው።


 

በዓሉ የመተዋወቅ ዕድልን በመፍጠር ወንድማማችነትን የሚያጎለብት ስለሆነ በጋራ ቀኑን የማክበሩ ልምድ ዳብሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም