ኢትዮጵያ በቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳደር በህንጻ ላይ በደረሰው ከባድ የእሳት አደጋ የተሰማትን ሀዘን ገለጸች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳደር በህንጻ ላይ በደረሰው ከባድ የእሳት አደጋ የተሰማትን ሀዘን ገለጸች
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 18/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳደር በህንጻ ላይ በደረሰው ከባድ የእሳት አደጋ የተሰማትን ሀዘን ገልጻለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የተጎጂ ቤተሰቦች እና በአሳዛኝ አደጋው ሰለባ ለሆኑ ዜጎች ልባዊ መጽናናትን እንደሚመኝ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከቻይና ህዝብ እና መንግስት ጋር በአጋርነት እንደምትቆምም ገልጿል።