በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል
ሰመራ፤ ሕዳር 18/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ በግንባር ቀደምትነት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ።
በሠመራ ከተማ "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለአፋር ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ፤በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ በግንባር ቀደምትነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በክልሉ የልማት ተግባራት የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና የህብረተሰብን ፍላጎት ባገናዘበ መልኩ መሰራታቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ እየተከናወነ ያለው ልማት ተስፋ ሰጪና የክልሉን የመበልጸግ አቅም ያሳየ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ለውጡን ተከትሎ በክልሉ የተሰሩት የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በስልጠናው የተገኘውን ተሞክሮ በማስፋት ለበለጠ ስራ መትጋት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በስልጠናው ከክልል፣ ከዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ከስልጠናው ጎን ለጎን የተሰሩ የልማት ስራዎችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።