በፕሪሚየር ሊጉ ምድረገነት ሽሬ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ምድረገነት ሽሬ ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሰባተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ምድረገነት ሽሬ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳንኤል ዳርጌ እና አቤል ማሙሽ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ምድረገነት ሽሬ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን በማስመዝገብ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ10 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።