በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ተካሄዷል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ14 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት በ16 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታውን ተከትሎ የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።