ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተካሄደ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 32ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
በትናንትናው እለት የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት መሰየምን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
ስብሰባው ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ስታስተናግድ አካታች እና በሚገባ የተሰናዳ ጉባኤ እንድታሳካ ለማረጋገጥ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት እንደነበርም ተገልጿል።