ቀጥታ፡

ዩጋንዳ ጅቡቲን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች  

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ሁለት ጨዋታ ዩጋንዳ ጅቡቲን 6 ለ 0 አሸንፋለች። 

ማምሻውን በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ብሪያን ኦልዋ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አርኖልድ ካዬምባ፣ ኡካሻ ጄምባ፣ ቶማስ ኦጌማ እና ፋሃድ ኢስማይል ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ዩጋንዳ በምድብ ሁለት በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። 

ዩጋንዳ በግማሽ ፍጻሜው ከአዘጋጇ ኢትዮጵያ ጋር እሁድ ሕዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ታደርጋለች።

በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሱዳን ብሩንዲን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ታንንዛያ በምድብ ሁለት 12 ነጥብ በማግኘት ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈች ሲሆን ለፍጻሜ ለማለፍ ከኬንያ ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም