ኢትዮጵያ ቡና ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ቡና ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ሸገር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ራምጌል ጀምስ በጨዋታ እና አቡበከር አዳሙ በፍጹም ቅጣት ምት ለቡናማዎቹ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ጀቤሳ ሚኤሳ ለሸገር ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የሸገር ከተማው ፍቅሩ ዓለማየሁ በሁለት ቢጫ በ57ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ከድል ጋር ታርቋል። ቡድኑ በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በስምንት ነጥብ ከ11ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ዝቅ ብሏል።