ቀጥታ፡

ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 ረቷል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቃልኪዳን ዘላለም በ77ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ፋሲል ከነማ በ15 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በበኩሉ በ13 ነጥብ ከሁለተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ዝቅ ብሏል።

በአሁኑ ሰዓት ሸገር ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም