ቀጥታ፡

ደቡብ ሱዳን ሩዋዳን በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ አንድ ጨዋታ ደቡብ ሱዳን ሩዋንዳን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

በአበበ በቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳንኤል ሎምቤ እና ፓኖም ጁዎ  የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የደቡብ ሱዳን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ሎምቤ ከራሱ የግብ ክልል አክርሮ በመምታት በተቃራኒ ቡድን ላይ ያስቆጠረው ጎል የጨዋታው የተለየ አጋጣሚ ነበር። 

ንሺሚዪማና ኦሊቨር ለሩዋንዳ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በውድድሩ የመጀመሪያ ድሏን ያስመዘገበችው ደቡብ ሱዳን በአራት ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

አራተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ሩዋንዳ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አምስተኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች።

በዚሁ ምድብ አስቀድማ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈችው አዘጋጇ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ በቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኢትዮጵያ ካሸነፈች የምድቡ መሪ ሆና ታጠናቅቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም