ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና መቻል በማሸነፍ መሪነቱን ያጠናከረበት ወሳኝ ድል አስመዘገበ  

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋናዊው ኮሊን ኮፊ ጨዋታው በተጀመረ በአንደኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መቻል መሪ ሆኗል።

አምበሉ ያሬድ ባየህ በ19ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና በ93ኛው ደቂቃ በጨዋታ ከመረብ ላይ ያሳረፋቸው ግቦች ሲዳማ ቡናን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስጨብጠውታል። 

በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ16 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል። 

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ12 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። 

የመቻሉ ጋናዊ ተጫዋች ኮሊን ኮፊ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ፈጣኑን ጎል ከመረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም