ቀጥታ፡

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

ማያ ፤ ሕዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሁሉም ዘርፎች ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።

በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ አስተዳደር የአመራር አባላት ስልጠና ተሳታፊዎች በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌና ጉርሱም ወረዳዎች ምርትና ምርታማነትን ለማጎልበት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።

"የመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የአመራር ስልጠና ላይ ከማያ ከተማ አስተዳደር፣ ከምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች የተውጣጡ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።


 

አመራሮቹ በወረዳዎቹ እየለሙ የሚገኙ የሙዝ ኢንሼቲቭ፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ የከብት ማድለብ ስራዎች፣ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የእምነበረድ ፋብሪካ የስራ እንቅሰቃሴን ተመልክተዋል ።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሐመድ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ በዞኑ በሁሉም ዘርፎች ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው።


 

በተለይም አርሶ አደሩን ከተረጂነት በማውጣት የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ የተለያዩ ኢንሼቲቮችን በመቅረፅ የተከናወኑት ተግባራት ውጤት አምጥተዋል ብለዋል።

በተለይም በሌማት ትሩፋት፣ በሙዝ ኢንሼቲቭ እና በስንዴ ምርት የተመዘገበው ውጤት መነቃቃትን የፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም