ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቦሌ ክፍለ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ ሜላት አሊሙዝ እና ምህረት አየለ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።  

የቦሌ ክፍለ ከተማዋ ብዙነሽ ቡልቻ በራሷ ላይ የባህር ዳር ከተማን ጎል አስቆጥራለች። 

በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ12 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ  ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በአራት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም