በዞኑ አርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማቱ የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ ለቤት እንስሳት ክትባት ትኩረት ተሰጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
በዞኑ አርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማቱ የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ ለቤት እንስሳት ክትባት ትኩረት ተሰጥቷል
አምቦ፤ ህዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ በዞኑ አርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማት የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ ለቤት እንስሳት ክትባት ትኩረት መሰጠቱን የምዕራብ ሸዋ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በዞኑ ለእንስሳት ክትባት አገልግሎት በተሰጠው ትኩረትም ባለፉት አራት ወራት 4 ሚሊዮን ለሚጠ የቤት እንስሳት ክትባት መሰጠቱን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡
በጽህፈት ቤቱ የእንስሳትና አሳ ጤና አስተባባሪ ዶክተር ሰኚ ሽመልስ ለኢዜአ እንደገለጹት አርሶ አደሩን ከእንስሳት ልማቱ የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ የእንስሳት ክትባት አገልግሎት ተሰጥቷል።
የእንስሳት በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል በበጀት ዓመቱ ከ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ እንስሳትን ለመከተብ ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።
በተለይም የቤት እንስሳትን ከተላላፊ በሽታዎች አስቀድሞ ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት ባለፉት አራት ወራት 4 ሚሊዮን የሚጠጉ እንስሳት መከተባቸውን ገልጸዋል።
ለእንስሳቱ የአባሰንጋ፣ አባጎርባ፣ ጎረርሳና ለሌሎች በሽታዎች መከላከያ ክትባት መሰጠቱን አመልክተዋል።
በተጨማሪም የበግና የፍየል በሽታዎች እንዲሁም የአፍሪካ የፈረሶች በሽታና የእብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን ጠቅሰዋል።
ክትባቱ የተሰጣቸው የቤት እንስሳት ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ942ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል።
ለዚህም ለእንስሳት ክትባት ትኩረት መሰጠቱና የህብረተሰቡ ግንዛቤ እያደገ መምጣቱን በምክንያትነት አንስተዋል።