ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊጉ ቤኔፊካ እና ዩኒየን ሴይንት ጊሎስ ድል አሸንፈዋል

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦  የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የአምስተኛ ጨዋታ መርሃ ግብር ዛሬ ማምሻውን ተጀምሯል።

በዮሐን ክራይፍ አሬና በተደረገ ጨዋታ ቤኔፊካ አያክስን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ሳሙኤል ዳህል እና ሊያንድሮ ባሬሮ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በውድድሩ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው ቤኔፊካ በሶስት ነጥብ 28 ደረጃ ላይ ይገኛል። በአንጻሩ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አያክስ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን 36ኛ ደረጃን ይዟል።

በሌላኛው መርሃ ግብር የቤልጂየሙ ዩኒየን ሴይንት ጊሎስ ከሜዳው ውጪ የተርኪዬውን ጋላታሳራይን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በራምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፕሮሚስ ዴቪድ በ57ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የጋላታሳራዩ አርዳ ኡናይ በ89ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በውድድሩ ሁለተኛ ድሉን ያገኘው ሴይንት ጊሎስ በስድስት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዟል።

በአንጻሩ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ጋላታሳራይ በዘጠኝ ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን በማስመዝገብ ደረጃውን ከ8ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በሶስት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም