ቀጥታ፡

የቀኑ መከበር ህብረብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ አንድነት እንዲጠናከር  አድርጓል

ጅማ ፤ሕዳር 16/2018 (ኢዜአ)፦ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር ህብረብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ አንድነት እንዲጠናከር ማድረጉ ተመለከተ።

በጅማ ከተማ አስተዳደር  የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ቀን በፓናል ውይይት ተከብሯል።

የጅማ ከተማ አስተዳደር አፈጉባኤ ተወካይ አቶ ፈክረዲን አብዱርቃድር  በወቅቱ እንዳሉት፤ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ቀን  መከበር በህብረብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ አንድነት እንዲጠናከር  አድርጓል።

ህዳር 29 የሚከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ቀን  የአንድነታችን መሰረት የሆነው ህገ መንግስት የጸደቀበትንና ለዘመናት የዘለቀው ወንድማማችነት   የሚጸናበት ነው ብለዋል።

ህብረብሔራዊነትን  መሰረት በማድረግ አንድነትን ማጽናትን አላማው ያደረገው ቀን መከበሩ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  እሴትን  ይበልጥ ለማስተዋወቅ የጎላ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰዋል።


 

የጅማ ከተማ አንድነትን  በህብረብሄራዊነት በማስተሳሰር  ልማት ላይ ማተኮሯን አንስተዋል።

 ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች  መካከል አርቲስት  ገብረመድን ከልክል  የብሔሮች ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን መከበር  አብሮነትን ለማጠናከር አቅም እንደሚሆን ጠቁመዋል።

የቀኑ መከበር  የተለያዩ  የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  ባህላዊ ጭፈራዎች፣ ምግቦች፣ የአልባሳት፣  የተለያዩ የአኗኗር  ስርአቶችንና  ባህላዊ እሴቶች  እርስ በርስ ለመተዋወቅ እድል ይፈጥራል ብለዋል።

ወይዘሮ ሱካሬ መሀመድ በበኩላቸው፤  ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች  በአብሮነት ለዘመናት በመኖራቸው ያካበቱትን  እሴት አደባባይ ወጥተው የሚያሳዩበት ቀን መሆኑን ተናግረዋል።

የቀኑ መከበር ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች   አብሮነታቸውን  ለማጠናከርና  በአንድነት  ለልማት የሚነሱበትን እድል እንደሚያሰፋው  አክለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም