ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ይርጋጨፌ ቡና ሁለተኛ ድሉን አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ይርጋጨፌ ቡና አዲስ አበባ ከተማን  1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አዲስ ዘውገ በ69ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።

አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ድሉን በማስመዝገብ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ8ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በሶስት ነጥብ የመጨረሻውን 14ኛ ደረጃ ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም