አዳማ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ተጀምሯል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ አዳማ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ በ75ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያገኘው አዳማ ከተማ በ12 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል።
በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በዘጠኝ ነጥብ ከ9ኛ ወደ 8ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።
በተያያዘም በአዲስ አበበ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ውብሸት ክፍሌ እና ቅዱስ ቂርቆስ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ፍቃዱ መኮንን ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው ወላይታ ድቻ በአምስት ነጥብ ደረጃውን ከ19ኛ ወደ 16ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው መርሃ ግብር የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን ከነጌሌ አርሲ ከምሽቱ 12 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።