በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሐግብር አዳማ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ምስር ኢብራሂም እና የልደታ ክፍለ ከተማዋ ሰርክዓለም ሻፊ በራሷ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቃልኪዳን ጥላሁን ለልደታ ክፍለ ከተማ ብቸኛውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥራለች።
በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አዳማ ከተማ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።
በአሁኑ ሰዓት ይርጋጨፌ ቡና ከአዲስ አበባ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።