ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ሶስተኛ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 16/2018(ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል። 

በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊርማዬ ከበደ እና ዝናሽ ሰለሞን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

መዳኒት አለሙ ለአርባምንጭ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች። 

በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉን ያገኘው ድሬዳዋ ከተማ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ በሰባት ነጥብ ከ9ኛ ወደ 10ኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም