ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ሕዳር 16/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን ጋር ዛሬ ማለዳ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጋር በቀጣናዊ የጸጥታ እና የበለጠ ትብብር ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም