ቀጥታ፡

ሱዳን ጅቡቲን አሸነፈች 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 15/2018 (ኢዜአ)፦ በ16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የምድብ ሁለት ጨዋታ ሱዳን ጅቡቲን 3 ለ 1 አሸንፋለች።

ማምሻውን በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤልሀሰን ሂልሚ ሀሰን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሳሚ ሀሰን እድሪስ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ዛሂር አስማር ኢክባል ለጅቡቲ ብቸኛውን ጎል በፍጹም ቅጣት ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

በምድቧ የመጀመሪያ ድሏን ያስመዘገበችው ሱዳን በሶስት ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጋለች።

በውድድሩ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደችው ጅቡቲ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አምስተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ዛሬ ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ታንዛንያ ብሩንዲን 5 ለ 0 አሸንፋለች። ብሄራዊ ቡድኑ በ12 ነጥብ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም